ብሪጅ

ወደ ብሪጅ እንኳን በደህና መጡ

ብሪጅ እኤአ በ 2004 የሽርክ ስራ ማህበር ሆኖ ተመሠረተ:: የማእድ ቤት፣ የቢሮ እና የቤት ፈርኒቸሮችን፣ በሮች፣ መስኮቶች፣ የበረንዳ እና የባልኮኒ መደገፊያዎችን እና የመሳሰሉትን በማምረት የጀመረው ብሪጅ እኤአ በ2010 ወደ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አደገ:: ብሪጅ በ21 ቋሚ እና በ3 ግዚያዊ ሠራተኞች ስራ የጀመረ ቢሆንም በአሁኑ ሠዓት ከ175 በላይ ሠራተኞች እና 63000000 ብር የሚገመት ንብረት አለው::

ብሪጅ በስራ መደቡ ላይ ሁሌም ስመጥር ከመሆኑም በላይ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ከቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ እና ከሌሎችም የስኬት እና የተሳትፎ ምስክር ወረቀቶች ተበርክቶለታል::

የብሪጅ ሠራተኞች በስራ መደባቸው ላይ በቂ ልምድ ያላቸው ሲሆን፡ ጥራት ያላቸው እቃዎችን ለማምረት እና ደምበኞቻቸው ጋር ባላቸው መልካም ግንኙነት ማንም ይመሠክራል። በልዩ ሁኔታዎች ላይ ብሪጅ ከክፍላቸው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ አዲስ ተመራቂ ተማሪዎችን ይቀጥራል። ምንግዜም የምንተጋው ደስተኛ ሠራተኞች እና የረኩ ደምበኞችን ለማፍራት ነው።

እቃዋቻችን በከፍተኛ ጥራታቸው ምንግዜም በደምበኞቻችን ተመራጭ ያደርጋቸዋል::  ብሪጅ ሁልግዜም በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ አሻራውን በማሳረፍ የማይዘናጋ ሚና ተጫውቷል። ይህ የማያቋርጥ ድጋፋችን የማይሰበር እና የማይላላ የቤተሰባዊ ግንኙነት ከህብረተሠቡ ጋር እንዲኖረን አድርጓል።

ብሪጅ በአሁኑ ስዓት በብዛት እና በፋብሪካ ደረጃ የአልሙኒየም የምግብ ሠሃኖችን/ቴክ አዌይ ቦክስ/ አልሙኒየም የምግብ መጠቅለያዋችን/አልሙኒየም ፎይል/ እና ዝገት አልባ ሲንኮችን/ስቴይንለስ ስቲል ሲንኮችን/ በማምረት ላይ ይገኛል:: በቅርብ ግዜ ደግሞ የስቲል ወንበሮች ጠረጴዛዎችን ለማምረት በዝግጅት ላይ ይገኛል:: ብሪጅ ምንግዜም በደምበኞቹ፡ ጥራት ባለው ምርትና ግዜውን በጠበቀ የላቀ መስተንግዶ ይታወቃል።